እዚህ በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ የተላላፊ በሽታዎች ምልክቶች መረጃ እናቀርባለን፡፡ እነዚህን በአፋጣኝ ማከም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም ጤናዎን ይጠብቃል እንዲሁም ሌሎች በበሽታው እንዳይጠቁ ያደርጋል፡፡
እዚህ በጣም አስፈላጊ ስለሆኑ የተላላፊ በሽታዎች ምልክቶች መረጃ እናቀርባለን፡፡ እነዚህን በአፋጣኝ ማከም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም ጤናዎን ይጠብቃል እንዲሁም ሌሎች በበሽታው እንዳይጠቁ ያደርጋል፡፡
የትኛውም አይነት ምልክቶች ካሉብዎ ወይም ጤንነት ካልተሰማዎ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡
በሙቀታማ በጋ ሌሊቶች በጣም ማላብ የተለመደ ነገር ነው፡፡ ይህ የመኝታ ቤት ከመጠን በላይ ከሞቀም የሚከሰት ነው፡፡ ነገር ግን፣ መደበኛ የሙቀት መጠን ባለበት ክፍል ውስጥ ከመጠን በላይ የሚያልብዎ ከሆነ የተላላፊ በሽታ መያዝዎን ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡
ከሌሊት ላቡ በተጨማሪ ትኩሳት ካለዎ እና ክብደት እየቀነሱ ከሆነ ወደ ሜዲክ ኸልፕ ይሂዱ፡፡
የሌሊት ላብ የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል
በቆዳ መቆጣት ወቅት ቀይ ክብ ነጥብ ወይም ማንኮፍኮፍ በቆዳ ላይ ይታያል ወይም ቆዳው በጣም ይደርቅ እና ይሰነጣጠቃል ወይም በጣም ያሳክካል፡፡ ይህ የተላላፊ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
ቆዳዎ ከተቆጣ ወይም ካሳከክዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡
የቆዳ መቆጣት እና ማሳከክ የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል
መቆረጦች፣ ጭረቶች፣ ወይም ንክሻዎች ቆዳን ሊጎዱ እና ቁስለት ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ በአግባቡ ያልዳነ ቁስል ልዩ አትኩሮትን ይፈልጋል፡፡
ክፍት ሆኖ የሚታይ ቁስል ካለብዎ፤ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡
ክፍት ሆኖ በቆዳ ላይ የሚታይ ቁስል ብዙውን ግዜ የጉዳት ምልክት ነው፡፡ በአግባቡ የማይድኑ ከሆነ፤ ይህ ማለት ምልክት ሊሆን ይችላል፡
በቀን ከሶስት ግዜ በላይ የአንጀት መታወክ ካጋጠምዎ ወይም ካስቀመጥዎ፤ ይህ ተቅማጥ ይባላል፡፡ ይህ የተላላፊ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡
ተቅማጥ ካለብዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡
በቂ ውሀ እና የተወሰነ መጠን ያለው ሻይ ይጠጡ፡፡
ሌሎችን መበከልን ለማስወገድ ሁልግዜም እጅዎን በሳሙና ይታጠቡ፡፡
ተቅማጥ የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል
ማስመለስ የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ማስመለስ የተላላፊ በሽታዎች ምልክት ሊሆንም ይችላል፡፡
የሚያስመልስዎ ከሆነ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡
በቂ ውሀ እና የተወሰነ መጠን ያለው ሻይ ይጠጡ፡፡
ሌሎችን መበከልን ለማስወገድ ሁልግዜም እጅዎን በሳሙና ይታጠቡ፡፡
ማስመለስ የተለያዩ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል
ለብዙ ሌሊቶች የመተኛት ችግር ካጋጠምዎ ወይም ማብራራት የማይችሉት አይነት ፍርሀት ይሰማዎ ከሆነ ይህ የአእምሮ ችግር ወይም ስቃይ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የሚታይ ምልክት ከሌለው ህመም ጋርም አብሮ ይሄዳል፡፡
በአግባቡ እየተኙ ካልሆነ ወይም እንግዳ የሆነ ህመም ከተሰማዎ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡
የመተኛት ችግር፣ ምክንያት አልባ ፍርሀት ወይም እንግዳ የሆነ ህመም የተላላፊ በሽታ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ከሌሎች ነገሮች መካከል፣ የሚከተሉትን ሊያመላክት ይችላል፡
በዚህ ገፅ ላይ በዋነኛነት የሚያገኙት መረጃ ስለ በጣም አስፈላጊ ስለሆኑት ተላላፊ በሽታዎች ይሆናል፡፡
እርግጥ ነው፤ ብዙ አይነት ምልክቶች አሉ፡፡ ህመም ከተሰማዎት እና ጤና ነክ የሆነ ጥያቄ ካሎት ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡