ከታች የተጠቀሱትን ምክሮች ከተከተሉ ራስዎን ከብዙ ተላላፊ በሽታዎች መጠበቅ ይችላሉ፡፡
ከተላላፊ በሽታ ራስን ለመጠበቅ በጣም ቀላሉ እና ውጤታማው መንገድ ሁልግዜ እና በደንብ እጅን በሳሙና መታጠብ መቻል ነው፡፡ ቢያንስ መፀዳጃ ቤት ደርሰው ከተመለሱ በኋላ እና ምግብ ከመመገብዎ በፊት ሁልግዜም እጅዎን ይታጠቡ፡፡
ሁልግዜ ገላዎን ይታጠቡ እንዲሁም ጥርሶን በቀን ሶስት ግዜ ይቦርሹ፡፡
መደበኛ የሆነ የሰውነት ንፅህና መጠበቅ ከበሽታ ይጠብቆታል፡፡ የጥርስ ህመም ካለብዎ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡
ብዙ በሽታዎችን በክትባት ማስወገድ ይቻላል፡፡ ሰዎች ብዙ በተከተቡ ቁጥር በትንሹ ይታመማሉ፡፡
የስዊዝ የጤና ባለስልጣን ለሚከተሉት ክትባትን ይመክራል (ጥቂቶቹን ለመግለፅ)፡
ለምክር ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ
ከኤድስ በተጨማሪ፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ብዙ በሽታዎች አሉ፡፡ በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ኮንዶምን በመጠቀም በጣም በተሻለ ሁኔታ ራስዎን መጠበቅ ይችላሉ፡፡ ለሴቶችም የሚሆን ኮንዶም አለ፡፡
በማእከሉ ውስጥ ኮንዶም ይሰራጫል ወይም ኬሚስቶች ፣ ፋርማሲ ውስጥ እና በአብዛኛዎቹ ሱፐር ማርኬቶች ውስጥ ይሸጣል፡፡
እፅ በሚወስዱበት ወቅት ጥቅም ላይ የዋለ መርፌ የሚጠቀሙ ከሆነ በደም አማካኝነት ለበሽታ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ሁልግዜም ንፁህ እና ጥቀም ላይ ያልዋለ መርፌ ይጠቀሙ፡፡
ነብሰ ጡር ከሆኑ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡ ባለሙያው እርሶ እና ልጅዎ ጤናማ ሆናችሁ የምትቆዩበትን መንገድ ከእርሶ ጋር ቅድመ ሁኔታዎችን ይነጋገራል እንዲሁም ከህክምናው ልዩ ባለሙያ ጋር እንዲገናኙ ቀጠሮ ይይዛል፡፡
ልጆችዎን በመደበኛነት በሜዲክ-ኸልፕ እንዲታዩ ያድርጉ፡፡ ሜዲክ-ኸልፕ በልጅዎ የምግብ አጠቃቀም እና እንክብካቤ ዙሪያ ሊረዳዎ ይችላል፡፡ በዚህም የተነሳ ልጆችዎ ጤናማ ሆነው ይቆያሉ እና በተገቢው መንገድ ያድጋሉ ፡፡