በበሽታ ለረጅም ግዜ እየተሰቃዩ ነበር? በየግዜው መድሀኒት ይወስዳሉ? በትውልድ አገርዎ ወይም በስደት ላይ እያሉ የህክምና እርዳታ አግኝተዋል?
እንደ ጎኖሪያ፣ ሲፍልስ ወይም ክላሚዲያ ያሉ በሽታዎች በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ ውጤቱ ሊያካትት የሚችላቸው ነገሮች ማዠት ፣ማሳከክ፣ መቁሰል ወይም በብልት አካባቢ ህመም መሰማት ናቸው፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት ምልክት ሳይኖርብዎ በበሽታው ተይዘው ሊሆንም ይችላል፡፡
በግብረ ስጋ ግንኙነት ከሚተላለፉ በሽታዎች ራስዎን ይጠብቁ፡፡ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ሁልግዜም ኮንዶም ይጠቀሙ፡፡ በማእከሉ ውስጥ ሊያገኟቸው ወይም ደግሞ ከኬሚስቶች ፣ ከፋርማሲ ወይም ከአብዛኞቹ ሱፐር ማርኬቶች ሊገዟቸው ይችላሉ፡፡
ምናልባት የትኛውንም አይነት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የሚተላለፍ በሽታ ምልክት ካለብዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡
ካለ ኮንዶም ከተፈፀመ የግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ በግብረ ስጋ ግንኙነት ምክንያት በሚተላለፍ በሽታ ስለመያዝዎ እርግጠኛ ካልሆኑ ለማማከር ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡ ምልክት እስከሚያዩ ድረስ አይጠብቁ፡፡
ኤች አይቪ በሽታን የመከላከል አቅምን የሚያዳክም ቫይረስ ነው፡፡ ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ ቫይረሱ በደምዎ ውስጥ ሊኖር ይችላል፡፡ መድሀኒት መውሰድ ካልጀመሩ ሰውነቶን ሊያዳክም ይችላል እስከ መታመም ደረጃ ሊያደርሶም ይችላል፡፡ ይህም ኤድስ ተብሎ ይጠራል፡፡
ይህ በሽታ የሚተላለፈው በደም፣ ያለ ኮንዶም በሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ ንፁህ ያልሆነ መርፌ በመጠቀም፣ ወይም ባልተወለደ ልጅ ላይ በቀጥታ ከእናት ወደ ልጅ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ይህ ቫይረስ ካለብዎ ምንም አይነት የበሽታ ምልክት ሳያሳዩ ወደ ሌሎች ሰዎችን ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡
ኤች አይቪ የሚድን በሽታ አይደለም፡፡ ነገር ግን መድሀኒቱ ቫይረሱን በመቆጣጠር እና ጉዳቱን በመቀነስ ያግዛል፡፡
ራስዎን ከኤች አይቪ/ኤድስ ይጠብቁ፡፡ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ሁልግዜም ኮንዶም ይጠቀሙ፡፡ በማእከሉ ውስጥ ሊያገኟቸው ወይም ደግሞ ከኬሚስቶች፣ ከፋርማሲ ወይም ከአብዛኞቹ ሱፐርማርኬቶች ሊገዟቸው ይችላሉ፡፡
በበሽታ መያዝን ለማስወገድ በደም ስር ለሚሰጡ መድሀኒቶች ሁልግዜም ንፁህ እና ጥቅም ላይ ያልዋለ መርፌ ይጠቀሙ፡፡
ያለ ኮንዶም ከተፈፀመ የግብረ ስጋ ግንኙነት በኋላ በኤችአይቪ/ኤድስም ሆነ በሌላ በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ መያዝዎን እርግጠኛ ካልሆኑ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ በመሄድ ይማከሩ፡፡ ምልክት እስከሚያዩ ድረስ አይጠብቁ፡፡
ቲቢ ያለባቸው ሰዎች ከሶስት ሳምንት በላይ ያስላሉ፣ ትኩሳት፣ የሌሊት ላብ ይኖራቸዋል፣ ወይም ክብደት ይቀንሳሉ፡፡ ቲቢ ጤነኛ የሆኑ ሰዎች ከህመሙ ጋር ያሉ ሰዎች ያሳሉበትን አየር ስበው ወደ ውስጥ ሲያስገቡ ሊተላለፍ ይችላል፡፡
ቲቢ አደገኛ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ በሽታ በፍጥነት ከተደረሰበት ሊድን ይችላል፡፡ ህክምናው ቢያንስ ስድስት ወር ይፈጃል፡፡
የትኛውም የቲቢ ምልክት ካለብዎ፣ ከዚህ ቀደም የቲቢ ህክምና አግኝተው ከነበረ፣ ወይም ከታመመ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ከነበርዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡
በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፍ- እንደ ጦርነት፣ ማምለጥ፣ በሰዎች መሰቃየት እና መደፈር አካልን ወይም አዕምሮን ያሳምማል፡፡ በከፍተኛ መጠን አልኮል ወይም ሌላ አይነት እፅ መጠቀም በራሱ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡
አብዛኞቹ የተጠቁ ግለሰቦች ስለ አዕምሮ ህመም ማውራት ከባድ ይሆንባቸዋል፡፡ ለሌላ በሽታ ትኩረት እንደምንሰጠው ሁሉ ለእነሱም ትኩረት መስጠት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
ሊሆን የሚችል የአዕምሮ ህመም ምልክቶች ውስጥ ለረዥም ግዜ እንቅልፍ ያለመተኛት፣ ቅዠቶች፣ እንግዳ የሆነ ህመም ወይም ሌሎች ችግሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
የአዕምሮ ስቃይ ሊታከም ይችላል፡፡ ሜዲክ-ኸልፕን ያግኙ፡፡
ይህ ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ የላይኛው የመተንፈሻ ክፍል ወይም ቆዳ ህመም ነው፡፡ ሁለት አይነት ናቸው፡ የጉሮሮ እና የቆዳ ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ፡፡
በዚህ የጉሮሮ በሽታ የተያዙ ሰዎች በጉሮሮ ህመም፣ ትኩሳት እና በመዋጥ ግዜ ህመም ይሰቃያሉ፡፡ የዚህ ጉሮሮ ህመም በጣም ጠቃሚው ምልክት ለመዳን አስቸጋሪ የሆነ ቁስል ነው፡ ክትባት በመውሰድ ራስዎን ከተላላፊው የጉሮሮ በሽታ መከላከል ይችላሉ፡፡
እርሶ ወይም ልጅዎ የዚህ ተላላፊ የጉሮሮ በሽታ ምልክት ከታየብዎ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ፡፡
እስካሁን ይህ የጉሮሮ በሽታ ይዞት የማያውቅ ከሆነ ክትባቱን ይውሰዱ፡፡ ወደ ሜዲክ-ኸልፕ ይሂዱ