የህክምና እንክብካቤ በስዊዘርላንድ

የህክምና እንክብካቤ በስዊዘርላንድ

በስዊዘርላንድ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው የህክምና እንክብካቤ የማግኘት መብት አለው፡፡ ለማንኛውም አይነት የበሽታ ምልክት በጥገኝነት መጠየቂያ ማእከሉ ውስጥ ወደሚገኘው ሜዲክ-ኸልፕ በቅድሚያ ይሂዱ፡፡

በመጀመሪያ ወደ አጠቃላይ ባለሙያው ይሂዱ፡፡

ስዊዘርላንድ ውስጥ የጤና ባለሞያው በህመም ወይም በአደጋ ግዜ በመጀመሪያ የሚያገኙት አካል ነው፡፡ ህክምና ያደርጉሎታል እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ ወደ ሆስፒታል ወይም ወደ ሌላ ልዩ ባለሙያ ይልኮታል፡፡

አጠቃላይ ባለሙያው በሽተኛውን እና ከዚህ ቀደም የነበረውን የህክምና ታሪክ ካወቀ የተሻለ ህክምና ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ ስለዚህ ሁልግዜም ወደ አጠቃላይ ባለሙያው መጀመሪያ ይሂዱ፡፡

Icon_Medic_Help.png

ህመም ከተሰማዎ በቀጥታ ወደ ሆስፒታል አይሂዱ፤ ይልቁንስ ወደ አጠቃላይ ባለሙያው ይሂዱ፡፡

Icon_Medic_Help.png

በድንገተኛ አደጋ ወቅት ወይም ለመውለድ በቀጥታ ወደ ሆስፒታል ይሂዱ፡፡

የህክምና እንክብካቤ በጥገኝነት መጠየቂያ ማእከሉ ውስጥ

ለጥገኝነት ጥያቄ አቅርባችሁ ከሆነ (ኤን ፐርሚት) የከለላ ፍላጎት(ኤስ) ወይም ጊዜያዊ ፈቃድ አግኝተው ከሆነ(ኤፍ) የግዛቱ ባለስልጣን የጤና ዋስትና ፖሊሲውን ይፈፅምቦታል፡፡ የነዋሪነት ፈቃድ ካልዎ( ወይም ፐርሚት) ለራስዎ የኢንሹራንስ ወጪ መሸፈን ሀላፊነት የሚወስዱት ራስዎ ኖት፡፡ ኢንሹራንስ የግድ ሊኖርዎ ይገባል፡፡

ዶክተሮች እና ሁሉም የህክምና ባለሙያዎች ለሙያዊ ሚስጥር መጠበቅ ተጠያቂ ናቸው፡፡ እንደታካሚነትዎ ስለ እርሶ ምንም አይነት መረጃ ለሶስተኛ ወገን እንዲያሳልፉ አይፈቀድላቸውም፡፡ ለዚህ የእርሶን ፈቃደኝነት ማግኘት አለባቸው፡፡